የተከበረች ኢትዮጵያን ለመገንባት መሰረት የጣለው ምክክር…

You are currently viewing የተከበረች ኢትዮጵያን ለመገንባት መሰረት የጣለው ምክክር…

AMN- ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ያካሄደችው ስኬታማው ሃገራዊ ምክክር የጋራ መግባቢያ ሃሳቦችን ማመንጨት የቻለ እና ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን ያረጋገጠ ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን ለረጅም ጊዜ በቆዩ አለመግባባቶች እና ልዩነቶች ላይ በመወያየት እና በመምከር የጋራ መፍትሄ ማምጣት እንደሚችሉ በተግባር አሳይተዋል።

የሃገራዊ ምክክር ጉባኤው የሀገሪቱን ሰላም፣ ዴሞክራሲ እና የጋራ ኑሮ ለማሻሻል የሚያስችል ታሪካዊ የምክክር ምዕራፍ ነው፡፡

ምክክሩ ዘላቂ ሰላምን ከማምጣት ባለፈ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን መሰረት የጣለ ሲሆን ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር የሚረዱ ሐሳቦችም ተንጸባርቀውበታል፡፡

ምክክሩ በስኬት መጠናቀቁም የኢትዮጵያውያን አሸናፊነትን ማሳያ ሲሆን ልዩነትን በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ ለችግሮች መፍትሄ መፈለግ እንደሚቻልም ማረጋገጫ ሆኗል፡፡

የምክክር ሂደቱ በሰለጠነ መንገድ የመወያየት ባህልን ያሳደገ፣ የኢትዮጵያውያን ድምጽ የተሰማበት፣ የሃገር ፍቅር ስሜትም የተንጸባረቀበት ነው፡፡

ከመላ ሃገሪቱ ከህዝቡ የተወከሉ 4 ሺህ ተመካካሪዎች በተሳተፉበት ታሪካዊው ሃገራዊ ምክክር ጉባዔ ስምንት ዋና ሃገራዊ አጀንዳዎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

ምክክሩ በኢትዮጵያ መልካም ተስፋዎች የታዩበት ሲሆን የምክክሩ ተሳታፊዎችም በሰለጠነና ግልጽ በሆነ መንገድ ሃሳባቸውን በማቅረብ ሃላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡

በዚህም ከ40 ቀናት በላይ በዘለቀው ሃገራዊ ምክክር ተሳታፊዎች በቀጣይ ለሰላም ግንባታ፣ ለሃገራዊ እቅድ እና ፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ የተለያዩ ምክረ-ሀሳቦችን አቅርበዋል፡፡

ሃምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም የጀመረው እንዲሁም መከባበርን እና መደማመጥን መርህ በማድረግ ሲካሄድ የቆየው ታሪካዊው የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ጉባዔ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም የመዝጊያ ስነ-ስርዓቱ መካሄዱ ይታወቃል፡፡

የሻምበል ምህረት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review