አገልግሎቱ በ6 ከተሞች ያስገነባቸውን 11 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ መሙያ ጣቢያዎች አስመረቀ

You are currently viewing አገልግሎቱ በ6 ከተሞች ያስገነባቸውን 11 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ መሙያ ጣቢያዎች አስመረቀ

AMN- ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ፣ ቢሾፍቱ ፣ አዳማ ፣ ባቱ፣ ሞጆ እና ሐዋሳ ከተሞች ያስገነባቸውን 11 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ማቻረጃ ጣቢያዎች አስመረቀ።

በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደው የምረቃ ሥነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው ፤ የመሠረተ ልማት ምረቃው ኢትዮጵያ ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ የምታደርገውን ስኬታማ ሽግግር የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ያላትን ታዳሽ ኃይል ለልማትና ለኢኮኖሚ እድገት በስፋት እየተጠቀመችበት እንደሚገኝ የጠቀሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ፣ ተቋሙ ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ከተማ ባስገነባቸው ቻርጅ መሙያ ጣቢያዎች አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሰዋል።

በዛሬው ዕለት ወደ ሥራ የገቡት ቻርጅ መሙያ ጣቢያዎች በአዲስ አበባ 5 ፣ በቢሾፍቱ 2 እንዲሁም በአዳማ፣ ባቱ፣ ሞጆ እና ሐዋሳ ከተሞች በእያንዳንዳቸው 1 ጣቢያ ሲሆኑ፤ በአንድ ጊዜ 96 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚያስችሉ መሆናቸውን ጌቱ ገረመው(ኢ/ር) ተናግረዋል።።

ከዚህ ቀደም የነበሩትን ጨምሮ ተቋሙ ባከናወናቸው የመሠረተ ልማት ማስፋፋት ሥራዎች በአሁኑ ወቅት በ14 ጣቢያዎች 150 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል አቅም መገንባቱ ተመላክቷል።

በታምሩ ደምሴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review