ራፊንሀ የስፔን ላሊጋ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተባለ

You are currently viewing ራፊንሀ የስፔን ላሊጋ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተባለ

AMN-ግንቦት 29/2017 ዓ.ም

የባርሴሎናው የፊት መስመር ተጫዋች ራፊንሀ የ2024/25 የውድድር ዘመን የስፔን ላሊጋ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል፡፡

ብራዚላዊው ኮኮብ በውድድር ዘመኑ ለባርሴሎና በላሊጋው 18 ግቦችን ሲያስቆጥር 10 ግብ የሆኑ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ ማቀበል ችሏል።

በሁሉም ውድድሮች ደግሞ 34 ግቦችን ሲያስቆጥር 22 ግብ የሆኑ ኳሶችን አማቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡

ባርሴሎና በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት የስፔን ላሊጋ ዋንጫን ሲያሳካ የራፊንሀ ሚና የጎላ እንደነበርም አይዘነጋም ፡፡

በሀና ታሪኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review