ፕሬዚደንቱ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ በኢራን – እስራኤል ጦርነት ሃገራቸው የሚኖራትን ሚና ይወስናሉ- ነጩ ቤተመንግስት

You are currently viewing ፕሬዚደንቱ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ በኢራን – እስራኤል ጦርነት ሃገራቸው የሚኖራትን ሚና ይወስናሉ- ነጩ ቤተመንግስት

AMN-ሰኔ 13/2017 ዓ.ም

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ በኢራን-እስራኤል ግጭት ውስጥ በቀጥታ ስለሚኖራቸው ሚና ከውሳኔ እንደሚደርሱ ነጩ ቤተ-መንግስት አስታውቋል።

በቤተ መንግስቱ ጋዜጣዊ መግለጫ የፕሬስ ሴክሬታሪ ኃላፊዋ ካሮሊን ሌቪት የትራምፕን መልእክት ግልፅ ያደረገች ሲሆን “በቅርቡ ከኢራን ጋር ሊኖር የሚችልን የድርድር እድል መሰረት በማድረግ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ በሁለቱ ሃገራት ጦርነት መካከል አሜሪካ ስለሚኖራት ሚና ከውሳኔ እደርሳለሁ” ማለታቸውን አስታውቃለች።

ቀደም ሲል የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምክትል ሚኒስትር ለቢቢሲ እንደተናገሩት ዩናይትድ ስቴትስ ጣልቃ ከገባች በአካባቢው የከፋ ነገር እንደሚፈጥር ተናግረው “ይህ የአሜሪካ ጦርነት አይደለም” ማለታቸው ይታወሳል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review