ለማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች በማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

You are currently viewing ለማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች በማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
  • Post category:ጤና

AMN – ታኀሣሥ 9/2018 ዓ/ም

የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዙሪያ ለማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ወይም ይዘት ፈጣሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ በስልጠናው ላይ ባስተላለፉት መልእክት በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት በተከሰቱ ወረርሽኞች ለማህበረሰቡን ግንዛቤ በማስጨበጥና የተሳሳቱ መረጃዎችን በማጥራት በሽታውን በመከለከልና በመቆጣጠር በሚደረገው ርብርብ ላይ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ አደገኛ ገዳይ በሽታ መሆኑን ያነሱት የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ አብቴ በላቦራቶሪ ምርመራዎች የተረጋገጠ መረጃዎች በየቀኑ እየወጠ ስለሆነ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ወይም ይዘት ፈጣሪዎች ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ለማህበረሰቡ እንዲያሰራጩና ተደራሽ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

የጤና ሚኒስቴር ለማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች የጋራ ፎረም ማደራጀቱ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ያነሱት የጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ጤና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ወቅታዊ እና እዉነተኛ የሆኑ የጤና መረጃዎችን ከጤና ሚኒስቴር የድረ-ገፅ አማራጮች እንዲጠቀሙ አሳስበዋል ፡፡

በተጨማሪም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የዘርፉ ባለሙያዎች በመጠየቅ ታማኝነትና ተከታታይነት ያላቸው ስራዎች በመስራት ማህበረሰቡ ፈጽሞ ሳይዘናጋ ራሱን እንድጠብቅ ሚድያዎች የማይተካ ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸዉ አፅንኦት ሰጥተዋል።

በስልጠናው በማህበራዊ ሚዲያ አንቂ እና ይዘት ፈጣሪዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች መሳተፋቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባጋራው መረጃ ገልጿል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review