በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ይጠበቃሉ

You are currently viewing በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ይጠበቃሉ

AMN ታኅሣሥ 18 ቀን 2018 ዓ.ም

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት መርሐግብር ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ይከናወናሉ። ቀን 9:30 ማንችስተር ሲቲ ወደ ሲቲ ሲቲ ግራውንድ አቅንቶ ኖቲንግሃም ፎረስትን ይገጥማል። ማንችስተር ሲቲ ጨዋታውን ካሸነፈ አርሰናል ጨዋታውን እስኪያከናውን የሊጉ መሪ የሚሆንበትን እድል ያገኛል።

ጥሩ ብቃት ላይ የሚገኘው የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን በሁሉም ውድድር ያደረጋቸውን ሰባት የመጨረሻ ጨዋታዎች አሸንፏል። የሊጉ መሪ አርሰናል በሜዳው ኤምሬትስ ብራይተንን ያስተናግዳል። መድፈኞቹ መሪነታቸውን ለማስጠበቅ ሦስት ነጥቡ ያስፈልጋቸዋል።

በዛሬው ጨዋታ ተከላካዩ ፒዬሮ ሂንካፒዬ መግባቱ አጠራጣሪ እንደሆነ ተገልጿል። ጨዋታው ምሽት 12 ላይ የሚጀምር ይሆናል።

ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ወልቭስን የሚገጥምበት ጨዋታም የዛሬ መርሐግብር አካል ነው። ሰሞነኛ ብቃቱ ጥሩ የሆነው የመርሲሳይዱ ክለብ የመጨረሻዎቹን ሦስት ተከታታይ ጨዋታዎች አሸንፏል። ጉዳት የገጠመው አሌክሳንደር ኢዛክ በዛሬው ጨዋታ አይሳተፍም።

ምሽት 12 ሰዓት በሚጀምረው በዚህ ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች ወደ ሜዳ ሲገቡ ከወራት በፊት በመኪና አደጋ ሕይወቱን ያጣው ዲያጎ ጆታ ልጆችን ይዘው ይገባሉ ተብሏል። የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ በቼልሲ እና አስቶንቪላ መሀከል ምሽት 2:30 ይከናወናል።

በኡናይ ኤምሬይ እየተመሩ የማይታመን የውጤት ጉዞ ላይ የሚገኙት ቪላዎች 10 ተከታታይ ጨዋታ አሸንፈዋል። ዛሬ በስታምፎርድብሪጅ ቼልሲን የሚገጥሙበት ጨዋታም በጉጉት ይጠበቃል።

በሌሎች ጨዋታዎች በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ብሬንትፎርድ ከ ቦርንማውዝ ፣ በርንሌይ ከ ኤቨርተን እንዲሁም ዌስትሃም ዩናይትድ ከ ፉልሃም ይጫወታሉ።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review