ኢትዮጵያ እና ሳውዲ አረቢያ በቱሪዝም ዘርፍ ያላቸው ግንኙነት እያደገ መምጣቱ ተገለጸ

You are currently viewing ኢትዮጵያ እና ሳውዲ አረቢያ በቱሪዝም ዘርፍ ያላቸው ግንኙነት እያደገ መምጣቱ ተገለጸ

AMN- ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው እለት የሳውዲ አረቢያ ቱሪስት አስጎብኚ ቡድንን ተቀብሎ አወያይቷል።

በዚህ ወቅት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር)፣ ኢትዮጵያ እና ሳውዲ አረቢያ በተለያዩ ዘርፎች የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት ያለቸው ሀገራት መሆናቸውን በማንሳት፣ የኢትዮጵያ መንግስት ለቱሪዝም ዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት ሁለቱ ሀገራት በዘርፉ ያላቸው መልካም ግንኙነት እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።

የቱሪዝም መዳረሻዎች በተሻለ ሁኔታ እየለሙ መሆናቸውንና መሰረተ ልማቶችም ተሟልተው ለጎብኝዎች ምቹ መሆናቸውን የገለጹት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ፣ ዘርፉን ይበልጥ በማሳደግ የሁለቱን ሀገራት ግንኙት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።

የሳውዲ አረቢያ ቱሪስት ቡድን አባልና የሶሻል መዲያ ባለሙያ አቶ አሊ ዳውድ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ እና ሳውዲ አረቢያ የጠበቀ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸው፣ ሁለቱን ሀገራት በቱሪዝም ዘርፍ ያላቸውን ግንኙት ለማሳደግ በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፉ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑንም በጉብኝታቸው ማረጋገጥ እንደቻሉ ጠቁመዋል።

የሳውዲ አረቢያ ቱሪስት ቡድን አባልና የጂቡቲ አየር መንገድ ማናጀር አቶ አሊድ አሊ፣ ኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ በትኩረት እየሰራች እንደሆነ መገንዘባቸውን ገልጸዋል፡፡

ለዓብነትም የአዲስ አበባ መዝናኛ ፓርኮች እና ሌሎች የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎቹ በፍጥነት እየለሙ መሆናቸውን አንስተዋል።

የቡድኑ አባልና የትረስት ትራቭል መስራች ሊና መሐመድ በበኩላቸው፣ በቱሪዝም ዘርፉ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነትን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፣ ኢትዮጵያ ያሏትን የቱሪስት መስህቦች እና ታሪካዊ ቅርሶች በዓለም እንዲታወቁ በትኩረት እንሰራለን ማለታቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review