አርሴናል አዳዲስ ተጫዋቾችን ሊያስፈርም እንደሚችል ሚካኤል አርቴታ ፍንጭ ሰጠ

You are currently viewing አርሴናል አዳዲስ ተጫዋቾችን ሊያስፈርም እንደሚችል ሚካኤል አርቴታ ፍንጭ ሰጠ

AMN – ታኅሣሥ 20/2018 ዓ.ም

በጥር ወር የተጫዋቾች የዝውውር ወቅት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሊያስፈርም እንደሚችል አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ ፍንጭ ሰጥቷል፡፡

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ባሳለፍነው ክረምት ስምንት ተጫዋቾችን ለማስፈረም 250 ሚሊዮን ፓውንድ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡

ባለፉት ሶስት ዓመታት በፕሪምየር ሊጉና በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን የቻለው አርሴናል ዘንድሮ የሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ እየመራ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ክለቡ በዚህ ዓመት በጉዳት እየተፈተነ ነው፡፡ ካይ ሀቨርዝ አሁንም ድረስ ወደ ሜዳ አልተመለሰም፡፡

እንደ ማርቲን ኦዴጋርድ፣ ቡካዮ ሳካ፣ ጋብሬል ማርቲኔሊ፣ ኖኒ ማዱኬን የመሳሰሉ ተጫዋቾችም ቢሆኑ በጉዳት ሳይሰለፉባቸው የቀሩ ጨዋታዎች በርካታ ናቸው፡፡

ቅዳሜ ምሽት ብራይተንን 2ለ1 ባሸነፉበት ጨዋታ ዴክላን ራይስ በቀኝ ተከላካይ ቦታ ለማጫወት የተገደደው አርቴታ “ጉዳት ላይ የሚገኙ ተጫዋቾች የሚመለሱበት ቀን ላይ ትኩረት አድርገናል፣ ከዚያ በኋላ መግዛት አለብን ወይስ የለብንም የሚለው ላይ ውሳኔ እናሳልፋለን፣ ሁልጊዜም ቢሆን የሚሆነው ስለማይታወቅ መዘጋጀቱ ጥሩ ነው” ብሏል ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ፡፡

አርሴናል ነገ ምሽት በፕሪምየር ሊጉ 19ኛ ሳምንት ከአስቶንቪላ ጋር በኤምሬትስ ጫዋታውን እንደሚያደርግ የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል፡፡

በታምራት አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review