AMN- ሐምሌ 11/2018 ዓ.ም

በ23ኛው የዓለም ዋንጫ ለደረጃ በተደረገ ጨዋታ እንግሊዝ ፈረንሳይን በማሸነፍ የነሐስ ተሸላሚ ሆናለች።
በማያሚ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ እንግሊዝ ከፍተኛ ብልጫ በመውሰድ 6ለ4 አሸንፋለች።

ቡካዮ ሳካ ሦስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል ፤ ዴክለን ራይስ ፣ ኢዝሪ ኮንሳ እና ጁድ ቤሊንግሃም ሌሎች የእንግሊዝን ግቦች አስቆጥረዋል።

በመጀመሪያው አጋማሽ 4ለ0 ተመርታ የነበረችው ፈረንሳይ በኪሊያን ምባፔ ሁለት ፣ በባርዲ ባርኮላ እና ኡስማን ዴምቤሌ አማካኝነት ያገኘቻቸው አራት ግቦች ልዩነት አልፈጠሩም።

ውጤቱን ተከትሎ እንግሊዝ 3ኛ ደረጃ ይዛ በማጠናቀቅ የነሐስ ሜዳልያ ተሸላሚ ስትሆን ፣ ለዋንጫ የተጠበቀችው ፈረንሳይ 4ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።