የጃፓን ኩባኒያዎች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ

You are currently viewing የጃፓን ኩባኒያዎች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ

AMN-ጥር 05/2018

የኢትዮ ጃፓን ቢዝነስ ፎረም የሁለቱ ሀገራት የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ኢንቬስተሮችን በማሳተፍ እየተካሄደ ይገኛል።

ይህ ፎረም በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማጠናከር የሚካሄድ ወሳኝ መድረክ ነው።

ፎረሙ በተለይ የጃፓን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እንዲሳተፉ በር የሚከፍት ነውም ተብሏል።

በፎረሙ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎንፌ(ዶ/ር) ባለፉት 5 ዓመታት በኢትዮጵያ እና ጃፓን መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ ማደጉን በመግለፅ የጃፓን ኢንቬስተሮች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢቨስትመን ሁኔታ እንዲጠቀሙም ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ ለውስጥና ለውጭ ኢንቨስተሮች ልዩ ማበረታቻ እያቀረበች ነው ያሉት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር) በኢትዮጵያ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለጃፓንም ይሁን ለሌሎች ሀገራት ኢንቨስተሮች ጥሩ ዕድል መፍጠሩንም አንስተዋል።

ጃፓን የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የንግድ እና ልማት አጋር መሆኗን የገለፁት እና ይህንን ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለፁት ደግሞ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ ኩኒሚትሱ አያኖ(ዶ/ር) ናቸው።

የኢትዮ ጃፓን የቢዝነስ ፎረም የኢንቨስትመንት ፍሰትን የመጨመር፣ የጃፓን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ማኑፋክቸሪንግ፣ ግብርና፣ እና አይሲቲ (ICT) ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ የማበረታታት እና የገበያ ትስስር የመፍጠር ዓላማን ያነገበም ነው።

በአሰግድ ኪ/ማርያም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review