የዚምባብዌ፣ የናይጄሪያ እና የናሚቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ አዲስ አበባ ገቡ

‎AMN ሐምሌ 19/2018

የዚምባብዌ፣ የናይጄሪያ እና የናሚቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ አዲስ አበባ ገብተዋል።

በ49ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ የአፍሪካ ሀገራት ልዑካን ቡድኖች አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።

‎በዚሁ መሠረት የዚምባብዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፕሮፌሰር አሞን ሙርቪራ፣ የናይጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ቢአንካ ኦዶሜጉ-ኦጁክው እንዲሁም የናሚቢያ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ንግድ ሚኒስትር ሰልማ አሺፓላ-ሙሳቪ አዲስ አበባ ገብተዋል።

‎ሚኒስትሮቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ሹም መላኩ በዳዳ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

‎49ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ሐምሌ 21 እና 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

‎በጉባኤው ለመሳተፍ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች እና የልዑካን ቡድን አባላትም አዲስ አበባ እየገቡ ነው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review