የኢኳቶሪያል ጊኒ፣ የቦትስዋና፣ የኮትዲቫር እና የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ‎በ49ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

AMN ሐምሌ 19/2018

የኢኳቶሪያል ጊኒ ሲሞን ኦዮና እሴኖ አንጌ፣ የቦትስዋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ‎ዶክተር ፌንዮ ቡታሌ፣ የኮትዲቫር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናያላ ካባ እና የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦሊቪዬ ንዱሁንግሬሄ በ49ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

‎በተጨማሪም የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢብራሂም አል-ባክሪ ኔይ ስብሰባውን ለመካፈል አዲስ አበባ ገብተዋል።

‎በ49ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ለመሳተፍ የአፍሪካ ሀገራት ልዑካን ቡድን አባላት አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።

‎በዚሁ መሠረት ‎የኢኳቶሪያል ጊኒ ሲሞን ኦዮና እሴኖ አንጌ፣ የቦትስዋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ‎ዶክተር ፌንዮ ቡታሌ፣ የኮትዲቫር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናያላ ካባ እና የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦሊቪዬ ንዱሁንግሬሄ እንዲሁም የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢብራሂም አል-ባክሪ ኔይ አዲስ አበባ ገብተዋል።

‎እንግዶቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ሹም መላኩ በዳዳ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

‎49ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ሐምሌ 21 እና 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review