የጸጥታና ደኅንነት ተቋማት 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ በስኬት እንዲጠናቀቅ በተዘጋጀው የጸጥታ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ

You are currently viewing የጸጥታና ደኅንነት ተቋማት 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ በስኬት እንዲጠናቀቅ በተዘጋጀው የጸጥታ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ

‎AMN-ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም

የጰጥታና ደኅንነት ተቋማት 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ በተዘጋጀው የጸጥታ ዕቅድ ላይ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ውይይት አካሂደዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ከፍተኛ መስዋዕትነት በመክፈል በርካታ የፀጥታ ሥራዎችን በመስራት በተለያዩ ጊዜያት በሀገራችን የተካሄዱ ታላላቅ ሁነቶች በስኬት እንዲጠናቀቁ ከፍተኛ ልምድ ያዳበሩ በመሆናቸው 39ኛውን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤንም ልምዳቸውን ተጠቅመው በስኬት እንዲያጠናቅቁ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።

የጰጥታና ደህንነት ተቋማት በሪፎርሙ የፈጠሩትን ከፍተኛ የሎጂስቲክስ፣ የቴክኖሎጂ፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል አቅም በማስተባበር ባደገና በተሟላ ዝግጅትና ቅንጂት በመስራት ጉባኤውን ማሳካት ይኖርብናል ብለዋል።

39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ የጸጥታና ደኅንነት ተቋማት የኦፕሬሽን ቲም በማቋቋም በአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያዋ እንዲሁም በመላው ሀገሪቱ የጋራ ኦፕሬሽን እንደሚካሄድ ኮሚሽነር ጄነራል ገልፀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በበኩላቸው የሀገራችንን ገጽታ ከፍ በሚያደርግ መልኩ በከፍተኛ ዲሲፕሊን እንግዶችን በመቀበል ቀድሞ በመዘጋጀትና የተጠናከረ የመረጃ ልውውጥ በማድረግ ጉባዔው በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

የጸጥታ ዕቅዱ በጸጥታና ደኅንነት ተቋማት በጋራ የተዘጋጀ እና ወቅታዊ፣ ውስጣዊና ውጫዊ የጸጥታ ጉዳዮችን በሚገባ በመተንተን የቀረበ በመሆኑ ጉባኤውን በስኬት ለማጠናቀቅ ከፍተኛ እገዛ እንዳለው በውይይቱ መነሳቱን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review