ባለፉት 6 ወራት 999 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መሰብሰበ ተችሏል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing ባለፉት 6 ወራት 999 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መሰብሰበ ተችሏል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN- ጥር 2 6/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ በበጀት አመቱ 6 ወራት በተለያዩ ብዝሃ ዘርፎች ከፍተኛ ውጤቶች መመዝገባቸዉን እና 999 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን አንስተዋል፡፡

ይህም የግብርናውን የአመቱን እቅድ 78 በመቶው ማሳካቱን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይም በሰብል፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እና በጥጥ ምርቶ አበረታች ውጤቶች መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

ለውጤቱ መሳካት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይም የማምረቻ ግብዓቶች መጨመር፣ የኮምፖስት ማዳበሪያ ዝግጅት ማደግና የማደበሪያ አቅርቦት መሻሻል ተጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም ከዚህ በፊት የማይታረሱ ቦታዎች ወደ ምርት መግባት፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ የበጋ እርሻ፣ የሌማት ትሩፋት እና ሌሎችም ተግባራት ተደማምረው ባለፉት 6 ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የምርት ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻሉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

በቀጣይ የግብርናውን ምርት ከዚህ የበለጠ ለማሻሻል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለእያንዳንዱ ምርትና የአፈር አይነት የሚስማማውን የማዳበሪያ አይነት ለመለየት የሚያስችል በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የናሙና ምርመራዎች እየተካሄዱ ናቸው ብለዋል፡፡

ከግብርናው በተጨማሪም በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን እና በአገልግሎት ዘርፎችም ባለፉት ስድስት ወራት ከፍተኛ ውጤቶች መመዝገባቸው ተብራርቷል፡፡

በአጠቃላይ ባለፉት 6 ወራት ተቋማት ያስመዘገቡት ውጤት በማክሮ ኢኮኖሚው ከተመዘገበው ውጤት ጋር ተዳምሮ የአመቱን እቅድ ለማሳካት የሚያነሳሳና ተስፋ ሰጪ አፈፃፀሞች መከናወናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመላክተዋል፡፡

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review