AMN ጥር 26/2028 ዓ.ም
6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባዉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፌዴራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በተመለከተም ባለፉት ስድስት ወራት 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ይህም ይህም ካለፈው ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ20 ነጥብ 6 ፐርሰንት እድገትም አለው ብለዋል።
ቀጥተኛ ብድሮች እና የመሳሰሉት ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ባለፉት ስድስት ወራት ገቢ ሲገኝ ለኢምፖርት የወጣው ወጪ ባለፈው ስድስት ወር 11 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ነውም ብለዋል።
በወጪና በገቢ መካከል በጎ ጅምሮች መታየታቸውን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢፖርት ከወጣው ወጪ ውስጥ 39 በመቶ የሚሆነው ለካፒታል ወጪ የተደረገ ነው ብለዋል።
አያይዘውም ኢኮኖሚው ምን ያህል ጤና ጉዞ ላይ እንዳለ አመላካች ነው፣3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ከውጭ ይገባ የነበረውንም በሃገር ውስጥ ማምረት መቻሉ ኢምፖርቱ የሚደረገውን ወጪ ለመቀነስ አግዟል ሲሉ አብራርተዋል።
በሚካኤል ኅሩይ