ተፎካካሪ ፓርቲዎችና መራጩ ሕዝብ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ንቁና ፍትሃዊ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የበኩሉን ሃላፊነት እንደሚወጣ ተገለጸ

You are currently viewing ተፎካካሪ ፓርቲዎችና መራጩ ሕዝብ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ንቁና ፍትሃዊ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የበኩሉን ሃላፊነት እንደሚወጣ ተገለጸ

AMN የካቲት 21/2018 ዓ.ም

ተፎካካሪ ፓርቲዎችና መራጩ ሕዝብ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ንቁና ፍትሃዊ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የበኩሉን ሃላፊነት እንደሚወጣ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር በመተባበር “የምርጫ ሂደትና የሚዲያ ሚና” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጁት የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ ተቋሙ የምርጫ ዴስክ ከማዋቀር ጀምሮ በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በምርጫዉ የሚሳተፉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርድ መመሪያ መሰረት የምርጫ ቅስቀሳ እንዲያደርጉና አጀንዳዎቻቸዉን ለህዝብ ተደራሽ እንዲያደርጉ ኤኤምኤን እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውጤታማና ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ጠንካራ መሰረት የሚጥል ምርጫ እንድታካሂድ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የበኩሉን ሚና እንደሚወጣም ዋና ስራ አስፈጻሚዉ አቶ ካሰሁን ጎንፋ ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡

በፓናል ዉይይቱ ላይ ላይ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ነዋይን ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ተወካዮች፣ የሚዲያ ተቋማት፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ሌሎች አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በሚካኤል ሂሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review