‎የሌማት ቱሩፋት የመሶባችንን ማዕድ ጉድለት የሚሞላ ነው

You are currently viewing ‎የሌማት ቱሩፋት የመሶባችንን ማዕድ ጉድለት የሚሞላ ነው

AMN- የካቲት 26/2018 ዓ.ም

‎የሌማት ቱሩፋት የመሶባችንን ማዕድ ጉድለት የሚሞላ ነው ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ።

‎በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 4ኛ ዓመት 3ኛ ዙር የሌማት ቱሩፋት ንቅናቄ የግብዓት ስርጭት ተካሂዷል።

‎በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ከተማ ከገጠር ብቻ የሚሸምት ከሆነ ማዕዱ ሊሞላ አይችልምና ከተማውም አምራች መሆን ያስፈልጋል ብለዋል።

የመዲናዋ ነዋሪዎች ባላቸው ውስን ቦታ በማምረት ከሸማችነት ወደ አምራችነት እንዲሸጋገሩ በተደረገው ጥረት አመርቂ ውጤት መምጣቱንም አንስተዋል።

‎የሌማት ቱሩፋት የሞሰባችንን ማዕድ ጉድለት የሚሞላ ነው ያሉት አቶ ሞገስ፣ አሁን ያለንበትን የኢኮኖሚ ስብራት መጠገን የምንችለው በዚሁ ግለት ጠንክረን ስንሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

‎አባቶቻችን በተለያዩ የአርበኝነት ስራዎች ሀገርን ከወራሪ በመጠበቅ ለትውልድ አስረክበዋል፤ የአሁኑ ትውልድ ደግሞ የኢኮኖሚ ስብራትን ለመጠገን መስራት አለበት ብለዋል አቶ ሞገስ።

‎በአመርቂ የስራ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚገኘው ክፍለ ከተማው በተለያዩ ስራዎች የተሻለ ውጤት አምጥቷል። ይህንን ለማጠናከርም የቤተሰብ የዶሮ ኬጂና መኖ ድጋፍ ማድረጉ ይበል የሚያሰኝ ነው ብለዋል።

‎ ድጋፍ የተደረገላቸው ዜጎችም የተሰጣቸውን ድጋፍ በአግባቡ ተጠቅመው ለውጤት መብቃት እንዳለባቸው ያሳሰቡት አቶ ሞገስ፣ በተለይም ራስችሁን ከመጥቀም ባለፈ ለገበያ ማረጋጋት ጉልህ ሚናችሁን መወጣት አለባችሁ ብለዋል፡፡

‎የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ በበኩላቸው አዲስ አበባ መሬት ተኮር የሆነውን ፖሊሲ በመቀየር ሰው ተኮር በማድረግ ነዋሪዎች በተለይም አርሶ አደሮች በዘርፋቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

‎ከ50 ሺህ የማይበልጡ የነበሩ አርሶ አደሮች በተሰራው ጠንካራ ስራ አሁን ላይ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የግብርና ቤተሰቦችን ማፍራት ተችሏል ብለዋል ።

‎የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በክፍለ ከተማው ከ12 ወረዳ ለተውጣጡ 1 ሺህ 200 ለሚሆኑ ዜጎች ባለ 50 ኬጂ በቁጥር 260 የሚሆኑ ኬጂዎች የዶሮ ጫጬት 11 ሺህ 500 እና መኖን ጨምሮ ስርጭት ተደርጓል ብለዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ዜጎችም ስለተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን ገልጸው፣ በተሰጣቸው ድጋፍ ጠንክረው በመስራት ውጤታማ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

በሄለን ጀንበሬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review