በአዲ አበባ ከተማ እየተገነቡ የሚገኙ የመኖሪያ ቤቶች አስፈላጊውን የመሰረተ ልማት የፋናስ አቅርቦትን እንዲሟላቸው ለማድረግ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

You are currently viewing በአዲ አበባ ከተማ እየተገነቡ የሚገኙ የመኖሪያ ቤቶች አስፈላጊውን የመሰረተ ልማት የፋናስ አቅርቦትን እንዲሟላቸው ለማድረግ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

AMN – የካቲት 28/2018 ዓ.ም

‎ከቤቶቹ ግንባታ ጎን ለጎን ደረጃውን የጠበቀ መሰረተ ልማት ተሟልተው እንዲገነቡ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን ተገልጸዋል፡፡

‎በአዲስ አበባ ከተማ የቤት አቅርቦት ጥያቄን ለመመለስ ከተማ አስተዳዳሩ በዘንድሮው በጀት ዓመት ብቻ አንድ መቶ ሺህ ቤቶችን ለመገንባት በትጋት እየሰራ ይገኛል፡፡

‎50 ሺህ የሚሆኑት በከተማ አስተዳደሩ በጀት ቀሪዎቹ 50 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ በመንግሥትና በግል አጋርነት የሚገነቡ ናቸው፡፡

‎እነዚህ ቤቶች አስፈላጊው መሰረተ ልማት ተሟልቶላቸው በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ይጠናቀቁ ዘንድ ርብርብ እየተደረገም ይገኛል፡፡

በም/ከንቲባ ማዕረግ ‎የአዲስ አበባ ከተማዋ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ባለፉት ዓመታት በከተማዋ የተገነቡ ቤቶች አስፈላጊው መስረተልማት ሳይሟላላቸው ለነዋሪዎች መተላለፋቸውን አንስተው ይህም በነዋሪው ላይ ከፍተኛ ጫና ስለማሳደሩ አንስተዋል፡፡

‎አሁን ይህንን ችግር ለመቅረፍ ቤቶቹ ከግንባታቸው ጎን ለጎን ከተማዋን የሚመጥን ደረጃውን የጠበቀ የመሰረተ ልማት ግንባታ ለማከናውን አስፈላጊው ስራ በቅንጅት እየተሰራ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡

‎በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በበኩላቸው የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት እንዳይኖር እና ቤቶቹን ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት ደረጀ ቱፋ ለቤቶቹ ግንባታ ስኬት ባንካቸው ከከተማ አስዳደሩሩ ጋር በትብር መስራን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡

‎የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ቅድስት ወልደ ጊዮርጊስ ባስተላለፉት መልዕክት የከተማው አስተዳደር ለዓመታት የቆየውን የከተማዋን ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለመመለስ ጠንካራ ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ኃላፊዋ አክለውም ‎በከተማ አስተዳደሩ የመንግስት በጀት የሚገነቡ ቤቶችም ሆነ ሌሎች የመሰረተ ልማት ችግሮችን ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ስለመሆኑም ገልጸዋል፡፡

‎ቤቶቹ በ6 ወራት ውስጥ በፍጥነት በተቀመጠለት ጊዜ ለማጠናቀቅ በአመራሩ ልዩ ክትትልና ድጋፍ በልዮ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

በሔለን ጀንበሬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review