የቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የኢፌዴሪ መሶብ አገልግሎትን ጎበኙ

You are currently viewing የቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የኢፌዴሪ መሶብ አገልግሎትን ጎበኙ

የቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የመሶብ አገልግሎትን ጎበኙ

AMN ሐምሌ 29/2018

የቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የኢፌዴሪ መሶብ አገልግሎትን ጎብኝተዋል።

የቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የተመራ የልዑካን ቡንድ በኢትዮጵያ የአምስት ቀናት የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ምሽት አዲስ አበባ መግባቱ ይታወቃል።

በዚህም መሰረት ሚኒስትሩና የልዑካን ቡድናቸው በኢፌዴሪ መሶብ አገልግሎት ጉብኝት እያደረገ ነው።

በኢፌዴሪ የመሶብ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ አለማየሁ ለልዑኩ ገለፃ አድርገውላቸዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው በገለፃቸው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአንድ ዓመት ውስጥ ከ200 በላይ የመንግሥት አገልግሎት በተሟላ መሰረተ ልማት ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ተችሏል ብለዋል።

ይህም የኢትዮጵያ ቁልፍ የኢኮኖሚ መሰረተ ልማት እንደሆነ በመግለጽ ቅሬታ የሚበዛበትን የመንግስት አገልግሎት ግልፅና ቀልጣፋ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን በማሳለጥ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል።

አገልግሎቱ የመንግስት ተቋማትን በማቀናጀት ተቋማት በአንድ ጣሪያ ስር ሁሉንም የመንግሥት አገልግሎት በፍትሐዊነት መስጠት አስችሏል ብለዋል።

የቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ኢኖቬሽን ሚኒስትሩና ልዑካቸው በቆይታቸው ከመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ጋር በሁለትዮሽና ትብብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ።

በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ የህዝብ አስተዳደር፣ ኢኖቬሽንና ስትራቴጂያዊ አስተዳደር ላይ ልምድ ይለዋወጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review