የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የብዝሀነት እና ግልጽነት ማሳያ ሆኖ እየተካሄደ መሆኑን ተመካካሪዎች ገለጹ

You are currently viewing የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የብዝሀነት እና ግልጽነት ማሳያ ሆኖ እየተካሄደ መሆኑን ተመካካሪዎች ገለጹ

AMN – ነሐሴ 1/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያዊያን በአንድ ጥላ ስር ተሰባስበው የትላንት የልዩነት መንስኤዎችን በመለየት፣ በዛሬው እውነታ ላይ በመመክር ለነገይቱ ሀገር ጠንካራ መሰረት ለመጣል ታሪካዊ ጉዞ ላይ ይገኛሉ።

የምክክር ሂደቱ ፍጹም ግልጽነትን እና ብዝሀነትን መለያው አድርጎ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ተመካካሪዎች ለኤ.ኤም.ኤን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ለዘመናት የዘለቁ ልዩነቶችን በራስ አቅም ለመፍታት የሚደረገው ጥረት ለሌሎች ሀገራትም በተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑን ተመካካሪዎቹ አንስተዋል።

የሀገራዊ ምክክሩ ስኬት የሀገርን ሁለንተናዊ ዕድገት የሚያረጋግጥ፣ ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋትን የሚያስፍን ቁልፍ ምዕራፍ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ምክክሩ ለቀጣዩ ትውልድ ተሻጋሪ እና አርአያነት ያለው ተግባር ሊሆን እንደሚገባው ያመለከቱት ተመካካሪዎች፣ ኢትዮጵያዊያን እያካሄዱት ያለው ይህ የምክክር ጉባኤ ከሀገር አልፎ በሌሎች የአፍሪካ እና የዓለም ሀገራት ጭምር እንደ መልካም ተሞክሮ የሚወሰድ መሆኑን ተናግረዋል።

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review