AMN መጋቢት 8/ 2018 ዓ/ም
የ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በስኬት ተከብሮ እንዲውል ከመጅሊስ አመራሮችና ከበዓሉ አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ተካሄዷል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ 1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል ።
መንግስትና የኃይማኖት ተቋማት በሰላም ዙሪያ በቅንጅት እየሰሩ በመሆናቸዉ የሀይማኖት ተቋማት የሰላም መገንቢያ ከመሆናቸው ባለፈ ለከተማው ተጨማሪ አቅም መፍጠራቸዉን ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸዉ በአሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መንገድ በስኬት እንዲከበር ሁሉም ሃላፊነቱነተ ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
የኃይማኖቱ አስተባባሪ ኮሚቴዎችም በአሉ ከሃይማኖታዊ እሴቱ ጎን ለጎን የሃገር ገጽታ የሚገነባበት በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአብሮነት እንዲያሳልፍ ጥሪ ማቅረባቸዉን የከተማዉ ፖሊስ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል፡፡