ማንሰን ኢንቨስትመንትስ የሴራሚክና የፖርሲሊን ምርቶችን በኢትዮጵያ ለማምረት የሚያስችለውን ስምምነት ፈጸመ

You are currently viewing ማንሰን ኢንቨስትመንትስ የሴራሚክና የፖርሲሊን ምርቶችን በኢትዮጵያ ለማምረት የሚያስችለውን ስምምነት ፈጸመ

AMN -መጋቢት 26/2018ዓ.ም

ማንሰን ኢንቨስትመንትስ ኃላ.የተ.የግል ኩባንያ ለኢትዮጵያ ገበያ ተስማሚና ደረጃቸውን የጠበቁ የሴራሚክና የፖርሲሊን ምርቶችን በኢትዮጵያ ለማምረትና በብቸኝነት ለማከፋፈል የሚያስችለውን ስትራቴጂካዊ ስምምነትን ከባይጂያ ሴራሚክ አምራች ድርጅት ጋር ተፈራረመ።

ስምምነቱ በዋናነት ማንሰን ኩባኒያ በባይጂያ ሴራሚክ አምራች ድርጅት በራሱ ዲዛይንና የጥራት ደረጃ በማምረት ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረብ የሚያስችለው ነው ተብሏል።

ስምምነቱ እያደገ በሚገኘው የኢትዮጵያ የግንባታ ዘርፍ የራሱን ጡብ በማሳረፍ ፣ የሐገር ውስጥ የገበያ ፍላጎትን በሐገር ውስጥ ምርት በመተካት ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬን የሚያስቀር መሆኑን የማንሰን ኢንቨስትመንት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳዊት እርገቱ ገልጸዋል።

በሐገር በቀል ምርቶች የገበያውን ፍላጎት በማሟላት ለአምራች ኢንደስትሪው ዘርፍ መነቃቃት የራሱን ሚና ይጫወታል ብለዋል።

የባይጂያን ስራ አስኪያ ጃንግ ሁዋ በበኩላቸው ድርጅታቸው በ50ሚሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት የኢትዮጵያን የሲራሚክ ፍላጎት ለመሸፈን እየሰራ መሆኑን ገልጸው ስምምነቱ የድርጅታቸውን የማምረት አቅም የሚያሳድግ መሆኑን ገልጸዋል።

ስምምነቱ የኢትዮጵያን ተኪ ምርት በማሳደግ የላቀ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

ሔኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review