በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የትንሳኤ ባዛር ተከፈተ

You are currently viewing በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የትንሳኤ ባዛር ተከፈተ

AMN- መጋቢት 28/2018 ዓ.ም

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የትንሳኤ በዓልን ምክኒያት በማድረግ የተዘጋጀ ባዛር ተከፍቷል፡፡

ባዛሩን ከፍተው ያስጀመሩት በምከትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንደሙ ሴታ ባስተላለፉት መልእክት፣ ከተማ አስተዳደሩ የነዋሪውን የኑሮ ጫና ለማቃለል ትላልቅ የገበያ ማዕከላትን መገንባትን ጨምሮ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ነጋዴዎችም ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ባለማድረግ በተመጣጣኝ ዋና ግብይት እንዲፈፅሙ ያሳሰቡት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ በነዳጅ አቅርቦት ምክንያትም የምርት አቅርቦት ችግር እንዳይፈጠር ሰፊ ሥራ መሠራቱንም አንስተዋል።

ባዛሮቹ ነዋሪው ምርትን ለበዓሉ በአካባቢው እንዲያገኝ ያስችላል ያሉት ደግሞ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ ናቸው፡፡

የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በበኩላቸው፣ በክፍለ ከተማው ተመሳሳይ ባዛሮች ሁልጊዜም በበዓላት ወቅት ሲዘጋጁ ስለመቆየታቸው አንስተው፣ ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በጽዮን ማሞ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review