AMN ግንቦት 15/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ትውልዱ ገብቶታል በሚል መሪ ቃል በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት የዛሬው የወጣቶች ድጋፍ እና ተነሳሽነት እጅግ አስደናቂ ነበር። እኛ ለኢትዮጵያ ብልጽግና በትጋት ስንሰራ፣ ወጣቱ ደግሞ የዚህ ስራ ፍሬ ተቋዳሽ እና የሀገሪቱን ብልጽግና የሚያጣጥም ይሆናል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ሀገራቸውን የሚወዱ እና ኢትዮጵያን ከፍ ለማድረግ የሚተጉ ወጣቶችን መመልከት፣ እኛም በበለጠ ትጋት እንድንሰራ ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥርልናል ብለዋል ከንቲባ አደነች።

ከዛሬው በተጨማሪ ሌላው ማሳያ፣ ሰሞኑን አዶናይ ብርሃነን የመሳሰሉ ወጣቶች እንደነ ዲላን ፔጅ ያሉ ታዋቂ የአጫጭር ማህበራዊ ሚዲያ ዜና አቅራቢዎችን ወደ ሀገራችን በማምጣት የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ ለመገንባት እያከናወኑት ያለው ተግባር የሚበረታታ እና ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ፣ ወጣቶቹን “በርቱ!” ልንላቸው ይገባል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክታቸውን አስተላፈዋል።