የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ሰሜን ኮሪያ ገቡ

You are currently viewing የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ሰሜን ኮሪያ ገቡ

AMN-ሰኔ 01/2018 ዓ.ም

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ከሰባት ዓመታት በኋላ ሰሜን ኮሪያ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንት ሺ በፒዮንጊያንግ ታርማክ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሰሜን ኮሪያው አቻቸው ኪም ጆንግ ኡን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የማርቺንግ ባንድ፣ የቻይናን እና የሰሜን ኮሪያን ባንዲራዎች የሚያወዛውዙ በርካታ ዜጎች በቦታው ተገኝተው በቀይ ምንጣፍ የታገዘ ደማቅ አቀባበል ማድረጋቸው ትኩረትን ስቧል።

ፕሬዚዳንት ሺ በየአመቱ ከሶስት እስከ አራት የውጭ ጉዞዎችን የሚያደርጉ ሲሆን ይኸኛው ግን ልዩ ትኩረት የሳበ የሁለትዮሽ ግንኙነትን መክፈቻ አዲስ ምዕራፍ አድርጓታል።

ሺ ጂንፒንግ በቻይና እና በሰሜን ኮሪያ መካከል ያለውን ግንኙነት ያደነቁ ሲሆን፣ግንኙነታቸው በአዲስ ታሪካዊ መነሻ ነጥብ ላይ እንደሚገኝ እና የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ጊዜውን የዋጀው አዲስ ተልዕኮ ያነገበ መሆኑም ታውቋል።

የፕሬዚዳንት ሺ የሰሜን ኮሪያ ጉብኝት ለሁለት ቀናት እንደሚቆይም ቢቢሲ ያጋራው መረጃ ያመላክታል።

በሚካኤል ህሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review