ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በወልድያ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ይመለከታሉ

AMN ሰኔ 2 /2018

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ለመመልከት ወልዲያ ከተማ መግባታቸውን ገልጸዋል።

ምከትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የታላቁ ራስ ዓሊ ከተማ፣ የየጁዎች ሥልጣኔ መገኛ፣ የአራቱ አውራ መንገዶች መገናኛ፣ ተራሮች እንደ ሐረግ ከተጋመዱባት፣ የሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ ንግድ ማዕከል በሆነችው የጥንቷ ገነቴ፣ የአሁኗ ወልድያ ከተማ ገብተናል ብለዋል።

ጎበዝና ቆንጆ ከሚወለዱባት፣ታሪክና ትውፊት ከተከማቸባት፣ ከመስጠት በስተቀር ስስት ከሌለባት ወልድያ ስንደርስ በአካባቢው ወግ መሰረት ደማቅ አቀባበል ላደረጉልን ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ ለካቢኔያቸው፣ ለወልድያ ከተማ ከንቲባ እና ለከተማዋ ነዋሪዎች ከልብ የመነጨ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ ያሉ ሲሆን በወልድያ በሚኖረን ቆይታ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን የምንጎበኝ ይሆናል ነው ያሉት፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review