AMN ሰኔ 17/2018

የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት እና የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ኢቫሪስት ንዲያሺሚዬ፥ በኢትዮጵያ በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ ያገኘውን ድል አስመልክተው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መግለጫ አስተላልፈዋል።
ፕሬዚዳንት ኢቫሪስት ንዲያሺሚዬ ባስተላለፉት የሰላምታና የደስታ መግለጫ መልዕክት፤ “የተከበሩ ወንድሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ብልጽግና ፓርቲ በምርጫው ላስመዘገቡት ስኬታማ ውጤት በአፍሪካ ኅብረት እና በቡሩንዲ ሪፐብሊክ ስም የተሰማኝን ልባዊ ደስታ እገልጻለሁ” በማለት የአጋርነትና የደስታ መልዕክታቸውን አጋርተዋል።