ለዘመናት የቆየው በኃይለ ቃል ጀምሮ በኃይል ርምጃ የመደምደም የኢትዮጵያን ስብራት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማቆም ያስፈልጋል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

You are currently viewing ለዘመናት የቆየው በኃይለ ቃል ጀምሮ በኃይል ርምጃ የመደምደም የኢትዮጵያን ስብራት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማቆም ያስፈልጋል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

AMN-ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም

ለዘመናት የቆየውን በኃይለ ቃል ጀምሮ በኃይል ርምጃ የመደምደም የኢትዮጵያን ስብራት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማቆም እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ምክክሩ ከተለመደው ጥቂት ሰዎች ከሚወስኑት በተለየ አቅጣጫ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለ4 ዓመታት መክረው እዚህ ደርሷል ብለዋል፡፡

በኃይለ ቃል ጀምሮ በኃይል ርምጃ መደምደም የኢትዮጵያ ስብራት ሆኖ ቆይቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ ይህን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መቋጨት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ለዚህም ሀገራዊው ምክክር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ነው የጠቀሱት፡፡

በርከት ያሉ ችግሮች አሳልፈናል ፣ በርከት ያሉ ያልተገቡ መከራዎች አሳልፈናል ሲሉ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ ይህን ፈተና ለመልካም ዕድል መጠቀም ከቻልን ለልጆቻችን የተሻለ ሀገር መስራት እንችላል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህን የተገኘውን መልካም ዕድል በታላቅ ኃላፊነት እንድተሰሩ በትህትና እጠይቃለሁ በማለትም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በታደሠ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review