AMN – ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም
የዘመናት የፖለቲካና የስርዓት ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመመለስና አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ለመክፈት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በይፋ ተጀምሯል።
በጉባኤው ማስጀመሪያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክከር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር)፣ የሀሳብ ልዩነት ውበታችን ነው፣ በመካከላችን የሚታዩ የሀሳብ ልዩነቶችና የተለያዩ አመለካከቶች የማንነታችንና የዴሞክራሲያዊ ህይወታችን ውበት ናቸው በማለት ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ ችግር የሚሆነው እነዚህን ልዩነቶች በምክክር ፋንታ በግጭት፣ በማግለልና በኃይል ለመፍታት መሞከሩ እንደሆነ አንስተዋል።

ጉባኤው እርስ በርስ ለመደማመጥና የታሪክ ጠባሳዎችን በጋራ ለመፈወስ ትልቅ ዕድል የሚሰጥ መሆኑን ተነግረዋል።
ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ(ፕ/ር) መላው ተሳታፊ ከጠባብ የቡድን ፍላጎት ወጥቶ ታላቋን ኢትዮጵያን ማዕከል በማድረግ በሆደ-ሰፊነት እንዲወያይ ጥሪ አቅርበዋል።
በታምራት ቢሻው