AMN- ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ እድገት ዛሬ በሚታዩ ለውጦች ብቻ የሚለካ ሳይሆን፣ ለመጪው ትውልድ ምን ዓይነት ከተማ ነው የሚረከበው የሚለው የእድገቱ ወሳኝ መለኪያ ነው።
አዲስ አበባ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከል ከመሆኗ ባሻገር፣ የፈጠራ፣ የባህል፣ የንግድና የዘመናዊ የከተማ ሕይወት ማዕከል ለመሆን ያላትን አቅም ማሳደግ እየቻለች ነው።
ይህንን በዘላቂነት ለማሳካትም የልማት ስራዎቿን ከከተማ ፕላን፣ ከባህልና ቱሪዝም፣ ከወጣቶች የሥራ ዕድል፣ ከዲጂታል አገልግሎቶችና ከዘላቂ ልማት ጋር በማቀናጀት ውጤታማ ስራዎችን እየሰራች ነው።
የዚህ እድገት ሂደትም የሰዎችን ፍላጎት በሚረዳ፣ የአካባቢን ሀብት በሚጠብቅና ለሁሉም ዕድል በሚፈጥር አካታች ዘላቂ ልማት መደገፍ ተችሏል።
አዲስ አበባ በ24/7 የምትሰራው የዛሬን ፍላጎት ለማሟላት እና የነገውን ዕድል ለማስፋት ነው።
ይህ አቅም እንደተለመደው በአመራር ቁርጠኝነት፣ በተቀናጀ አስተዳደርና በዜጎች ተሳትፎ ሲደገፍ፣ ከተማዋ ለነዋሪዎቿ የተሻለ ሕይወት ከመፍጠር ባለፈ ለሌሎች ከተሞችም ተሞክሮዋን ማካፈልን ትቀጥላለች።

ይህች ከተማ ወደ ተሻለ ነገ የምትጓዘው በህዝብ ትጋትና በጋራ ጥረት ነው። የለውጧ ሞተር ነዋሪዎቻችን እና ትጉህ የለውጥ መሪዎች ሲሆኑ፣ የእድገቷ መሠረት የጋራ ተሳትፎና ትጋት ነው።
የወደፊቷ ብርሃንም ዛሬ በሥራ ላይ የሚውሉ ሐሳቦች፣ የሚፈጠሩ ዕድሎችና ለሁሉም የሚጠቅም ልማት መሆናቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ፡ የማትቆም፣ የማትደክም፣ ሁሌም ወደ ፊት የምትገሰግስ ከተማ፡