ከኢትዮጵያዊ እና ሩሲያዊ ቤተሰቦች የተወለደው የሙዚቃ ባለሙያ የነበረው ነርሲስ ናልቫንዲያን መኖሪያና የቅርስ ቤት ታድሶ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

You are currently viewing ከኢትዮጵያዊ እና ሩሲያዊ ቤተሰቦች የተወለደው የሙዚቃ ባለሙያ የነበረው ነርሲስ ናልቫንዲያን መኖሪያና የቅርስ ቤት ታድሶ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

AMN- ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም

ከኢትዮጵያዊ እና ሩሲያዊ ቤተሰቦች የተወለደውና በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ አሻራ ያሳረፈው የቀድሞው የሙዚቃ ባለሙያ ነርሲስ ናልቫንዲያን መኖሪያና የቅርስ ቤት በሰላም ኢትዮጵያ አማካኝነት ታድሶ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

በ1929 ዓ.ም የተገነባው ይህ ታሪካዊ የቅርስ ቤት በውስጡ የስዕል ማሳያ ጋለሪን፣ እንዲሁም ሌሎች የጥበብ ሥራዎች መለማመጃዎችን አካቶ ለባለሙያዎች ክፍት መደረጉን የሰላም ኢትዮጵያ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ መንግሥቴ ገልጸዋል።

ነርሲስ ናልቫንዲያን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የመጀመርያዎቹ ዓመታት የሙዚቃ ክፍሉን የመሩ ሲሆን፣ ለያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት መመስረትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

በተጨማሪም እንደ ጥላሁን ገሠሠ፣ ዓለማየሁ እሸቴ እና ዳዊት ይፍሩ ያሉ በርካታ አንጋፋ ድምፃውያንንና የሙዚቃ ባለሙያዎችን አሰልጥነዋል።

የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት አርቲስት ዳዊት ይፍሩ፣ ይህን መኖሪያ ቤት ለአምሳ ዓመታት ያህል እንደሚያውቁት ገልጸው፤ ታሪካዊው ቤት በዚህ መልኩ ታድሶ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ለሙዚቃ እድገት መልካም አስተዋጽኦ እንዳለውና የነርሲስ ናልቫንዲያን ውርስ (ሌጋሲ) በዚህ መልኩ መቀጠሉ ለሁሉም ክብር መሆኑን ተናግረዋል።

ሰላም ኢትዮጵያ በሲውድን ሀገር የተጀመረ እና ከ20 ዓመታት ጀምሮ በባህል፣ በኪነ ጥበብ እና አፍሪካዊ ጉዳዮች ላይ እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው።

በየምስራች ተረክበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review