አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ያልተቀበሉ ሀገራት ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን?

You are currently viewing አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ያልተቀበሉ ሀገራት ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን?

AMN- የካቲት 17/2018 ዓ.ም

የቀድሞው የእንግሊዝ የፋይናንስ ሚኒስትር እና አሁን የዓለማችን ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋም ኦፕን ኤ አይ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ የሆኑት ጆርጅ ኦስቦርን፣ ለዓለም ሀገራት አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል፡፡

በሕንድ ዴልሂ እየተካሄደ ባለው የ2026 የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተፅዕኖ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ የተገኙት ኦስቦርን፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ኤ አይ)ን የማይቀበሉ ሀገራት የገጠማቸውን አደገኛ ዕጣ ፈንታ ገልጸዋል፡፡

በዚህም “ወደ ኋላ አትቅሩ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ካልተጠቀማችሁ ደካማና ድሃ ሀገር ሆናችሁ ትቀራላችሁ፤ የሰለጠነ የሰው ኃይላችሁም የተሻለ የቴክኖሎጂ ዕድል ፍለጋ ሀገሩን ጥሎ ይሰደዳል” ብለዋል፡፡

ብዙ ሀገራትም በዚህ ታላቅ የቴክኖሎጂ አብዮት ሳንቀድም አንቀርም በሚል ስጋት ውስጥ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

ዓለም በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ እንደ ኦፕን ኤ አይ ያሉ እና በቻይና የኤአይ ቴክኖሎጂዎች መካከል መከፈሏን እና ሀገራትም ከሁለቱ አንዱን ለመምረጥ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ሀገራት በሌሎች ቴክኖሎጂዎች ላይ ጥገኛ መሆን ቢያሰጋቸውም፣ ሳይጠቀሙ መቅረት ግን የከፋ ብሔራዊ ውድቀትን እንደሚያስከትልባቸው አስረድተዋል ሲል ዘ ጋርዲያን ዘግቧል።

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review