የከተማ ነዋሪዎችን የኑሮ ዘይቤ ለመቀየርና የምርት ባህልን ለማሳደግ የሌማት ትሩፋት ትልቅ አስተዋጽዖ አለው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing የከተማ ነዋሪዎችን የኑሮ ዘይቤ ለመቀየርና የምርት ባህልን ለማሳደግ የሌማት ትሩፋት ትልቅ አስተዋጽዖ አለው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ

AMN – ግንቦት 9/ 2018 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት የከተማ ነዋሪዎችን የኑሮ ዘይቤ ለመቀየርና የምርት ባህልን ለማሳደግ የሌማት ትሩፋት ትልቅ አስተዋጽዖ አለው ብለዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሐረር ከተማ እየተከናወኑ ያሉትን የማር፣ የወተትና የዶሮ እርባታ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ተዘዋውረን ጎብኝተናል ብለዋል።

በከተማው በኢኒሼቲቩ በግለሰብና በመንግሥት ደረጃ ሼዶችን በመገንባት የማር፣ የወተት፣ የእንቁላልና የአሳ መንደሮችን የማቋቋም ሥራ በስፋት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል አቶ ተመስገን።

እንደ ሀገር የአመጋገብ ስርዓታችንን ከመሰረቱ ለመቀየር እና በምግብ እራስን ለመቻል ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ይህ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የእንሳት፣ የዶሮና ዓሳ ዝርያ ማሻሻልና መኖ ማቀነባበሪያዎች ላይም ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ይገኛል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review