ኢትዮጵያውያን በብሄራዊ ጥቅም መዳረሻዎች ላይ ያላቸውን የጋራ ግንዛቤ እንዲያጠናክሩ የመገናኛ ብዙሃን ሚና ከፍተኛ ነው

You are currently viewing ኢትዮጵያውያን በብሄራዊ ጥቅም መዳረሻዎች ላይ ያላቸውን የጋራ ግንዛቤ እንዲያጠናክሩ የመገናኛ ብዙሃን ሚና ከፍተኛ ነው

AMN ግንቦት 12/2018

ኢትዮጵያውያን በብሄራዊ ጥቅም መዳረሻዎች ላይ ያላቸውን የጋራ ግንዛቤ እንዲያጠናክሩ መገናኛ ብዙሃን ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን “ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙሃን ሚና” በሚል ርዕስ በጋራ ያዘጋጁት መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ለማስገንዘብ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

በመድረኩ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፋሲካው ሞላ፣ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የስራ ሃላፊዎች፣ የመገናኛ ብዙሃን የስራ ሀላፊዎች እና ጋዜጠኞች ታድመዋል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ መገናኛ ብዙሃን ከብሄራዊ ጥቅም ማስጠበቅ አንጻር ያላቸውን ሚና በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም ኢትዮጵያውያንን በጋራ ሊያቆሙ ከሚችሉ ጉዳዮች መካከል አንዱ ብሄራዊ ጥቅም መሆኑን አንስተዋል።

ኢትዮጵያውያን በብሄራዊ ጥቅም መዳረሻዎች ላይ ያላቸውን የጋራ ግንዛቤ እንዲያጠናክሩ መገናኛ ብዙሃን ከፍተኛ ሚና አላቸው ብለዋል።

7ኛውን ጠቅላላ ምርጫን የተመለከተ ዘገባ ሲሰሩም የብሄራዊ ጥቅም ማስጠበቂያ መንገድ መሆኑን ሊያረጋግጥ በሚችል መልኩ መስራት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።

በመሆኑም መገናኛ ብዙሃን ምርጫን በተመለከተ በሚዘግቡት ዘገባ ከምርጫ ባሻገር መሆኑን በመረዳት መሆን አለበት ነው ያሉት።

ከፓናሉ ተሳታፊዎች በምርጫው ወቅት የመገናኛ ብዙሃንና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚናን የተመለከቱ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የተሰነዘሩ ሲሆን በፓናሊስተቶቹ እና በመገናኛ ብዙሃን የስራ ሀላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ በሰጡት አስተያየት ምርጫውን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሚዘጋጁ መሰል ስራዎች ይጠናከራሉ ማለታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።

See less

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review