AMN ግንቦት 28/2016
ሴቶች በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በመራጭነትና በታዛቢነት አበረታች ተሳትፎ ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ገለፀ።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የነበረውን አጠቃላይ የተሳትፎ ሂደት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር ገነት ስዩም በመግለጫቸው፤ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ፌዴሬሽኑ የበኩሉ ድርሻ ተወጥቷል ብለዋል።
በዚህም የፌዴሬሽኑ አባላት ገለልተኝነታቸውን ጠብቀው የታዛቢነት ሚናቸውን በአግባቡ እንደተወጡ ተናግረዋል።
ፌዴሬሽኑ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አጠቃላይ ከ14 ሺህ በላይ ታዛቢዎችን በማሰማራት 25 ሺህ 384 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የመታዘብ ስራ ማከናወኑን ጠቁመዋል።
የሴቶች ተሳተፎ ከቀደሙት የምርጫ ጊዚያቶች ሲነፃፀር መሻሻል ማሳየቱ ገልጸው፤ በጠቅላላ ምርጫው በመራጭነትና በታዛቢነት አበረታች ተሳትፎ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።