የቻይና ልዑክ አባላት የአዲስ አበባን የልማት ስራዎች ጎበኙ

You are currently viewing የቻይና ልዑክ አባላት የአዲስ አበባን የልማት ስራዎች ጎበኙ

AMN – ሰኔ 3/2018 ዓ.ም

የቻይና ቤጂኒንግ አድሚኒስትሬሽን ኢንስቲትዩት ልዑክ ቡድን አባላት በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ የልማት ስራዎችን ጎበኙ፡፡

የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ የአንድነት ፓርክንና በቅርቡ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገውን የእንጦጦ ቀጨኔ ወንዝ ዳርቻ ልማት ተመልክተዋል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አዲስ አበባ የመጡት ቻይናውያኑ ባለሙያዎች ዛሬ ተዟዙረዉ የከተማዋን የልማት ስራዎች የጎበኙ ሲሆን በተመለከቱት የልማት ስራም መደነቃቸውን ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ እና በቻይናው ቤጂንግ አድሚንስትሬሽን ኢኒስቲትዩት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ስልጠናም ሰሞኑን በቻይናውያኑ ባለሙያዎች ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

ከቻይናው ቤጂንግ አድሚኒስትሬሽን ኢንስቲትዩት የመጡት ከፍተኛ ባለሙያዎች ፣ ለአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ከፍተኛ አመራሮች እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት ለተወጣጡ አመራሮችና ተጋባዥ እንግዶች ነው ስልጠናውን የሰጡት፡፡

በየሺዋስ ዋለ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review