ይህንን ፅኑ ህዝብ ለመካስ ያስቀመጥናቸውን ግቦች በተሟላ መልኩ ለማሳካት ከመላው አመራራችን ጋር ተግባብተናል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ይህንን ፅኑ ህዝብ ለመካስ ያስቀመጥናቸውን ግቦች በተሟላ መልኩ ለማሳካት ከመላው አመራራችን ጋር ተግባብተናል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN-ሰኔ 03/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላፉት መልዕክት ፣ ዛሬ በምርጫ ሥራዎቻችን አፈጻፀምና የድህረ ምርጫ ሥራዎቻችን በውጤታማነት በመከወን የያዝናቸውን ግቦች በተሟላ መልኩ ከማሳካት አንፃር የተገኙ ዉጤቶችን ከመላው የከተማችን አመራሮች ጋር ገምግመናል ብለዋል።

7ኛውን ጠቅላላ ሃገራዊ ምርጫ በስኬት እንዳይጠናቀቅ ለማደናቀፍ በውጭም በውስጥም በጋራ በማበር በሚደያ ዘመቻዎች እና በተለያዩ ቅስቀሳዎች ሰላም የማደፍረስ ዝግጅቶችና ትንኮሳዎች ተደርገው ሳይሳካላቸው በኢትዮዽያ ታሪክ ትልቅ እድገት የታየበት ዴሞክራስያዊ፥ ሰላማዊና ተዓማኒ ምርጫ በማካሄድ ኢትዮዽያዊን በፅናት አዲስ ታሪክ ፅፈዉ ኢትዮጲያ መርጣለች፥ ኢትዮጵያ አሸንፋለች ብለዋል።

እንደሃገር ያሳካነው እጅግ ውጤታማ እና ታሪካዊ ምርጫ የህዝባችን ፣የአመራራችን፣ የአባሎቻችን ፣የደጋፊዎቻችን፣የሲቭክ ማህበራት ፣ የሚድያዎቻችን፣ ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም በገለልተኝነትና በከፍተኛ ዲሲፕሊን ትልቅ ሃገራዊ ሃላፊነታቸዉን የተወጡት የፀጥታ አካላትና የምርጫ ቦርድ በጥቅሉ ሁሉም ባለድርሻ አካል እንደ ሀገር ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላንን ቁርጠኝነትና በጋራ ያሳካነው ግብ መሆኑን ተግባብተናል ሲሉ ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች ፣ ለዚህም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት እናመሰግናለን ብለዋል።

የድህረ ምርጫ ስራዎቻችን በውጤታማነት በመፈፀም ይህንን ፅኑ ህዝብ ለመካስ ያስቀመጥናቸዉን ግቦች በተሟላ መልኩ ለማሳካት ከመላው አመራራችን ጋር ተግባብተናል ሲሉ በመልዕክታቸው ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review