በመንገድ ግንባታ ላይ የሚስተዋሉ መጓተቶችን ለማረም እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አሳሰበ

You are currently viewing በመንገድ ግንባታ ላይ የሚስተዋሉ መጓተቶችን ለማረም እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አሳሰበ

AMN – ሰኔ 4/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ በመንገድ ግንባታ እና ጥገና ስራዎች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማረም እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የመሰረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳስቧል፡፡

የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ከአየር ጤና- ካራ – ወለቴ እና የአውቶቢስ ተራ – መሳለሚያ- 18 ማዞሪያ የመንገድ ግንባታ ሂደትን የመስክ ምልክት አድርገዋል።

ቋሚ ኮሚቴው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የ2018 በጀት አመት 11 ወራት የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ስራዎችን ጨምሮ የእቅድ አፈጻጸም ላይ ግብረ- መልስ ሰጥቷል።

የሕዝብ ጥያቄ የተነሳባቸው የመንገድ ፕሮጀክቶች ምላሽ እንዲያገኙ በትኩረት መስራት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ግዛቸው አይካ (ዶ/ር) አሳስበዋል።

ባለስልጣኑ የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ በቅንጅት መስራት እንደሚገባውም አንስተዋል።

በመንገድ ግንባታ እና ጥገና ስራዎች ላይ የሚስተዋሉ መጓተቶችን በማረም ፍጥነት እና ጥራት ላይ ያለውን መሻሻል አጠናክሮ መቀጠል ይገባልም ብለዋል።

የህብረተሰብ ጥያቄ የነበረባቸው የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ የተሰጠው ፈጣን ምላሽ አበረታች መሆኑንም ሰብሳቢው ገልጸዋል፡፡

የመሰረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላትም በተደጋጋሚ ቅሬታ የሚነሳባቸው የመንገድ ግንባታ እና የጥገና ስራዎች ላይ ባለስልጣኑ ትኩረት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙህዲን ረሻድ ፤ በከተማዋ የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ስራዎች ላይ ያሉ ጉድለቶችን በማረም በቀጣይም በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል፡፡

ባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ ለዓመታት የመልካም አስተዳደር ችግር ያለባቸው 9 የመንገድ ፕሮጀክቶች መፍትሔ እንዲያገኙ ማስቻሉንም ገልጸዋል፡፡

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review