AMN- ጥቅምት 16/2019 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገር ሉአላዊነት ፣ የህዝብ ሰላምና የጽናት ምልክት በመሆን ታሪካዊ ግዴታውን በላቀ ጀግንነትና ታማኝነት እየተወጣ ይገኛል።
ሠራዊቱ የሀገርን ድንበር ከማስከበር ባለፈ በልማትና ህዝባዊ አግልግሎቶች ላይ እያሳየ ባለው ንቁ ተሳትፎ የህዝብ የቁርጥ ቀን አለኝታነቱን አስመስክሯል።
መከላከያ ሠራዊቱ የሀገርን ድንበርና የህዝብን ደህንነት ለማስከበር የሚያደርገው ተጋድሎ፣ የሀገሪቱን ታላቅነትና ጽናት የሚያንጸባርቅ ነው።
የጽናትና የጀግንነት ተምሳሌት የሆነው የሀገር መከላከያ ሠራዊት በማንኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አልፎ የሀገርን ሰላምና አንድነት ማስከበር ችሏል። በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ወቅት ከህዝብ ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የህዝብ አለኝታነቱን አረጋግጧል።

የሠራዊቱን የመዋጋትና የቴክኖሎጂ አቅም በማሳደግ የሀገርን ደህንነት አስተማማኝ በሆነ ደረጃ ላይ ለማድረስ የሚያስችሉ ዘመናዊ አደረጃጀቶችና ስልጠናዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍና በአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይ ያሳየው እጅግ የካበተ ልምድና የላቀ ምግባር የሀገራችንን ስም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ አድርጎታል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሀገር ህልውና መሠረት፣ የሰላም ዘብና የኢትዮጵያውያን አንድነትና ብዝሃነት ውብ ማሳያ ነው፡፡
በታምራት ቢሻው