AMN-ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም
የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪዎች በአካል ተገኝተን የተመለከትነው ስራ እጅግ አስደናቂ ነው ሲሉ በቅርቡ የተመረቀውን የወንዝ ዳርቻ ልማት አድንቀዋል።
በቅርቡ የተጠናቀቀው ከቀጨኔ በአምባሳደር ኢሬቻ እስከ ባምቢስ የተዘረጋው የወንዝ ዳርቻ ልማት የሀገራችን የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪ ቲክቶከሮች ጎብኝተዋል።
በቦታው ተገኝተው የተሰራውን ድንቅ ስራ የተመለከቱት እነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪ ቲክቶከሮች ”በአካል ተገኝተን የተመለከትነው ስራ እጅግ የሚያስደንቅ እና ከተማችን አዲስ አበባ የደረሰችበትን ፈጣን ዕድገት በግልፅ የሚያሳይ ነው ”ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም የከተማዋን አስገራሚ ለውጥ እና በመሰራት ላይ ያለውን የልማት ስራ ዘመኑ ባመቻቸው የማህበራዊ ሚዲያ አማራጭ በመጠቀም በሀገር ውስጥ እና በመላው አለም ለሚኖረው ህዝብ ማድረስ እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

ከቀጨኔ በአምባሳደር በኢሬቻ እስከ ባምቢስ የተዘረጋውና ለከተማዋ ተጨማሪ ውበት እና ምቾት ያጎናፀፈው ይህ ፕሮጀክት 351 ሄክታር ስፋት ያለውና 10 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ሲሆን፣ የተለያዩ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶችንና የሕዝብ መገልገያዎችንም በውስጡ ማካተቱን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።