
AMN – ታኅሣሥ 25/2017 ዓ.ም
ሃሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጅ የነበረ አንድ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የወረዳ ጽ/ቤት ሰራተኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
ከሰኔ 2016 ዓ.ም ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል መሸጋገሩ ይታወሳል፡፡
ይህንን ተከትሎ በአገልግሎት ላይ እንዳይውሉ በታገዱ ካርዶች የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ወረዳ 13 ጽ/ቤት የሆነ የነዋሪነት አገልግሎት ቡድን ኬዝ 2 የዲጂታል ምዝገባ ባለሙያ የነበረው አቶ ባጫ ኤጀታ ሃሰተኛ ሰነድ እያዘጋጀ መሆኑ ለክፍለከተማው የተቋሙ ጽ/ቤት በደረሰ ጥቆማ ባለሙያው በፀጥታ ሃይል ክትትል በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል።
በተደረገው ብርበራ ከተጠርጣሪው ጋር ህገወጥ ማነዋል መታወቂያ ብዛት 22 ፣ አንድ ያላገባ ማንዋል ካርድ፣ አንድ ማህተም እንዲሁም ከ100 በላይ የተለያዩ ሰዎች ፎቶግራፍ በኤግዝቢትነት ተይዞ በፖሊስ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ የኤጀንሲው መረጃ ያሳያል።