ኢትዮጵያ ከለውጡ በኋላ በዲፕሎማሲው መስክ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር የሚያስችሉ ስኬታማ ተግባራትን አከናውናለች

You are currently viewing ኢትዮጵያ ከለውጡ በኋላ በዲፕሎማሲው መስክ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር የሚያስችሉ ስኬታማ ተግባራትን አከናውናለች

AMN – የካቲት 2/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ከለውጡ በኋላ በዲፕሎማሲው መስክ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር የሚያስችሉ አመርቂ ተግባራትን ማከናወኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ፡፡

ብልፅግና ፓርቲ ባካሄደው ሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ በተለያዩ መስኮች የተገኙ ውጤቶችን የሚያስቀጥሉ ውሳኔዎች አስተላልፏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ፓርቲው ባሳለፋቸው ውሳኔዎች ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያ የብልጽግና የውጭ ግንኙነት ዋና መርህ አገራዊ ጥቅምን ማስጠበቅና ከአካባቢው አገሮች ጋር በጋራ መልማትና ማደግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ብልጽግና ከጎረቤት አገራት ጋር የጋራ ልማትና ዕድገትን ለማረጋገጥ አበክሮ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአካባቢው በጋራ ለማደግና ለመልማት የያዘውን ግብ ለማረጋገጥም ትኩረት መስጠቱን ገልጸው፤ የጎረቤት አገራትን ሰላም ለመረጋገጥ የተከናወኑ የሰላም ማስከበር ተግባራትም ከፍተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት በግልጽ አቋሟን ማራመድ የጀመረችው በብልጽግና ዘመን መሆኑን አስታውሰው፤ በዚህ ረገድ የተሄደበት መንገድ ብሔራዊ ጥቅማችንን በአግባቡ ለማስከበር የቻልንበት ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአካባቢው ያላትን ተፅእኖ ፈጣሪነት በመጠቀም ለቀጣናው ሁለንተናዊ ዕድገትም በቁርጠኝነት እየሰራች እንደምትገኝ አብራርተዋል።

እንደ አገር የፖለቲካ የኢኮኖሚና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች አዎንታዊ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

ዜጎች በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ መብታቸውና ክብራቸው እንዲጠበቅ በተሰሩ ስራዎች ለውጥ መገኘቱንም ማስረዳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review