በአዲስ አበባ ከተማ በጎ ፍቃደኝነትን ባህል ማድረግ ተችሏል

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ በጎ ፍቃደኝነትን ባህል ማድረግ ተችሏል

AMN—ሀምሌ 1/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡ ከ2ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞች የሥራ ስምሪት ሰጥቷል፡፡

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ አስራት ንጉሴ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር 18 የሚሆኑ የስራ መስኮች ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ኮሚሽኑ ተቋቁሞ ወደ ስራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በጎ ፍቃደኞችና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እያደገ መምጣቱን እና በጎ ፍቃደኝነትም ባህል እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።

የብዙዎችን እንባ ያበሰ፣ ለሀገር ዋጋ የከፈሉ አባቶችን የሚገባቸውን ክብር የሰጠ እና የበርካቶችን ጓዳ የሞላ ውጤታማ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

ኮሚሽኑ በክረምት የበጎ ፍቃድ መርሐ ግብር ከ9.4 ቢሊዮን ብር በላይ የመንግስት ሀብትን በበጎ ፍቃድ ለመሸፈን አቅዶ እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።

በደሳለኝ ሙሐመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review