የ21 ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ በሚደረጉ 2 ጨዋታዎች ይጀምራል

You are currently viewing የ21 ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ በሚደረጉ 2 ጨዋታዎች ይጀምራል

AMN – የካቲት 24/2017 ዓ.ም

ቀን 9:00 ሰዓት ሲል በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ስታዲየም ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮ ኤሌክትሪክ በአዳማ ከተማ መሸነፍ እና የኢትዮጵያ ቡና መቻልን ማሸነፍ ጨዋታውን ተጠባቂ አድርጎታል።

ምሽት 12:00 ሰዓት ሲል ሲዳማ ቡና ከሃድያ ሆሳዕና ይጫወታሉ።

ከመሪው ኢትዮጵያ መድን በ4 ነጥብ ዝቅ ብለው 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ሃድያ ሆሳዕናዎች ጨዋታውን አሸንፈው ከመሪው ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ሲጫወቱ፣ ሲዳማ ቡናዎች ደረጃቸውን ለማሻሻል ወደሜዳ እንደሚገቡ ይጠበቃል ።

ሊጉ ከነገ በስትያም ሲቀጥል ረፋድ 3፡30 ሰዓት ስሁል ሽረ ከአምናው ሻምፒዮን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሚገናኙ ሲሆን፣ 9:00 ሰዓት ላይ ደግሞ መቀሌ 70 እንደርታ ከሀዋሳ ከተማ፣ አዳማ ከተማ ከአርባ ምንጭ ከተማ ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

ፋሲል ከነማ ከባህር ዳር ከተማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወላይታ ድቻ የሐሙስ መርሃ ግብሮች ሲሆኑ፣ መቻል ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እና መሪዉ ኢትዮጵያ መድን ከድሬዳዋ ከተማ በሚያደርጉት ጨዋታ የ21ኛ ሳምንት የሚጠናቀቅ ይሆናል።

በሀና ታሪኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review