የኮሪደር ልማት ተነሺዎች ምትክ የመስሪያ ቦታ ተረከቡ

You are currently viewing የኮሪደር ልማት ተነሺዎች ምትክ የመስሪያ ቦታ ተረከቡ

AMN- ሚያዝያ 01/2017

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካሳንቺስ አካባቢ የንግድ ሱቅ የነበራቸው ነጋዴ የኮሪደር ልማት ተነሺዎች ምትክ የመስሪያ ቦታ በለማው ካዛንቺስ ላይ ተረከቡ::

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካዛንቺስ አካባቢ በቀበሌ ንግድ ቤት ሲሰሩ የነበሩ የልማት ተነሺዎች ግልፅና ይፋዊ በሆነ መልኩ እጣ በማውጣት በዘመናዊ መልኩ የተገነቡ የንግድ ሱቆችን የተረከቡ መሆኑን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አዲሱ ሻንቆ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

በዛሬው እለት የንግድ ሱቃቸውን የተረከቡት በጽህፈት መሳሪያ፣ በህንፃ መሳሪያ፣ በመብራት እቃዎች፣ በአገልግሎት ንግድ እና በሌሎች የሙያ መስኮች የተሰማሩ መሆናቸውም ተገልጿል።

በቀጣይም እንደአስፈላጊነቱ ተጨማሪ መስሪያ ቦታዎች እየተገነቡ ቀሪ ነጋዴዎችን ፍትሃዊ በሆነ አግባብ በእጣ የማከፋፈሉ ስራ እንደሚቀጥልም ከክፍለ ከተማው ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያስረዳል::

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review