ሰልጣኝ ኦፊሰሮች በአንድነትና በመተባበር የሚሰጣቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ

You are currently viewing ሰልጣኝ ኦፊሰሮች በአንድነትና በመተባበር የሚሰጣቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ

AMN-ግንቦት 16/2017 ዓ.ም

ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ6ኛ ዙር እጩ ፓራ-ሚሊተሪ ሰልጣኝ ኦፊሰሮች በሀገራዊ አንድነት እና መሰረታዊ የመደመር ጽንሰ ሃሳብ ላይ ገለጻ ተደርጓል።

በመድረኩም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ፣ “የመደመር እሳቤ” መነሻ ሃሳብ እንዲሁም “የለውጥ ቀጣይነት እና የፓርቲ ሚና” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስዳደር ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ ለሰልጣኞቹ አቅርበዋል።

በመድረኩ ላይ ሰልጣኝ ኦፊሰሮቹ የቀረበው ሰነድ በመደመር እሳቤ እና ለውጥ ላይ የነበራቸውን ግንዛቤ እንዳሰፋላቸው ገልጸዋል። በቀጣይም ተቋሙ የሚጥልባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት እንደተዘጋጁ ተናግረዋል።

ሰልጣኝ ኦፊሰሮቹ ለሚሰጣቸው ኃላፊነት የተናጠል ህይወት መርህ ተላቀው በአንድነትና በመተባበር የመደመር እሳቤን በመከተል በጋራ በመስራት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክት ተላልፏል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review