በቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች ከተቀመጠላቸው የዋጋ ተመን በላይ በሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ የእርምት እርምጃ እየተወሰደ ነው

You are currently viewing በቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች ከተቀመጠላቸው የዋጋ ተመን በላይ በሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ የእርምት እርምጃ እየተወሰደ ነው

AMN-ግንቦት 24/2017 ዓ.ም

በቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች ምርት የሚያቀርቡ ነጋዴዎች ከተቀመጠላቸው የዋጋ ተመን በላይ ለመሸጥ የሚያደርጉትን ጥረት ለመቆጣጠር የእርምት እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ኤ ኤም ኤን በጀሞ አንድ እና በአየር ጤና አደባባይ የሚገኙ የቅዳሜ ገበያዎችን ቃኝቷል፡፡

በእነዚህ ገበያዎች ላይ ምርታቸውን ይዘው የቀረቡ ነጋዴዎች ጥራቱ የተጠበቀ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እያቀረቡ እንደሚገኙ ገልጸው የተረጋጋ ግብይት እንዲኖር ሚናቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከሌሎች የገበያ ስፍራዎች ከነበረው ዋጋ በተሻለ መልኩ በቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኘን ነው ያሉት ደግሞ ሃሳባቸውን ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የሰጡ ሽማቾች ናቸው፡፡

በእነዚህ በቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች ላይ ምርት የሚያቀርቡ ነጋዴዎች ምርታቸውን በተቀመጠላቸው የዋጋ ተመን መሸጥ ቢጠበቅባቸውም አልፎ አልፎ ከተለጠፈው ዋጋ በላይ ለመሸጥ የሚደረግ ጥረት ይስተዋላል፡፡

በተቀመጠው ዋጋ ለሸማቹ ምርታቸውን እንዲያቀርቡም ቁጥጥር እና ክትትል እንደሚደረግ እና ይህን በማያደርጉ ምርት አቅርቢዎች ላይ የእርምት እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝም ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review