ፖርቹጋል ስፔንን በማሸነፍ የ2024/25 የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ሻምፒዮን ሆናለች።
ዛሬ ምሽት በአሊያንዝ አሬና ስፔንን ከፖርቹጋል ያገናኘው የፍጻሜ ጨዋታ በፖርቹጋል አሸናፊነት ተጠናቋል።
የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ በመደበኛው 90 ደቂቃ እንዲሁም በተጨማሪ 30 ደቂቃ 2 ለ 2 አቻ መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መለያ ምት አምርተዋል።
በጨዋታው የፖርቹጋልን ግቦች ኑኖ ሜንዴዝ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሲያስቆጥሩ የስፔንን ግቦች ዙቢሜንዲና ኦያርዛባል ከመረብ አሳርፈዋል።
በመለያ ምት ፖርቹጋል 5 ለ 3 በማሸነፍ የ2024/25 የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ዋንጫ ባለቤት ሆናለች።