የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ የቢሾፍቱ ከተማ ኮሪደር ልማት ያለበትን ደረጃ መመልከታቸዉን ገልጸዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ወደ መላው የኢትዮጵያ ከተሞች ተስፋፍቶ ህዝባችንን ተጠቃሚ እንዲያደርግ በጠቅላይ ሚኒስትራችን ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተሰጠን ተልእኮ መሰረት የቢሾፍቱ ኮሪደር ልማት የደረሰበትን ጀረጃ ተዘዋዉረን ተመልክተናል ብለዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ስራው ተጀምሮ እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ የከተማ አስተዳደሩ ያከናወነው ስራ የሚበረታታ መሆኑንም ገልጸዋል።
ቀሪ ስራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቀው ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ለማድረግ በትብብር እንደሚሰሩም ጠቁመዋል።