ለህክምናው ዘርፍ 130 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ሀብት እየተበጀተ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing ለህክምናው ዘርፍ 130 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ሀብት እየተበጀተ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ
  • Post category:ጤና

AMN ሰኔ 16/2017

መንግስት ለህክምናው ዘርፍ 130 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ሀብት እየበጀተ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የጤና ባለሞያዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት የጤናውን ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

በዚህም ባለፉት አመታት ወደ ለጤና ዘርፉ እየመደበ ያለውን በጀት እያሳደገ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከጥቂት አመታት በፊት በቀጥታ ለጤናው ዘርፍ ይመደብ የነበረው ሀብት 70 ቢሊየን ብር ገደማ እንደነበር አስታውሰው፤ በአሁኑ ወቅት መንግስት 130 ቢሊየን የሚጠጋ ሀብት መመደቡን አስታውቀዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ባለፈው ዓመት መንግስት 9 ቢሊዮን ብር ለመድሃኒት ግዥ ድጎማ ማድርጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

መንግስት ለህክምናው ዘርፍ የሚያወጣው ወጪ ከየትኛውም ጎረቤት ሀገራት እንደሚበልጥም ተናግረዋል።

በጤናው ዘርፍ መንግስት ለግንባታ የሚያወጣውን ወጪ የትኛውም ጎረቤት ሀገር እንደማያወጣ ጨምረው አንስተዋል፡፡

ምንም እንኳን ለጤናው ዘርፍ የሚበጀተው በጀት እያደገ ቢሆንም ካለው ፍላጎት አንጻር ገና መሆኑን ጠቅሰዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review